
ባሕር ዳር፡ መስከረም 22/2013ዓ.ም (አብመድ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ቲሊሊ ከተማ የሚገኘው ኪሊ መስክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ በአዲስ መልክ ተገንብቷል።
ከዚህ ቀደም ትምህርት ቤቱ ለመማር ማስተማር ሂደቱ አስቸጋሪ እና የማይመጥን ተማሪዎች በፈራረሰ እና በወደቀ፣ በር እና መስኮት በሌለው፣ ዝናብ እና ፀሐይ በሚፈራረቅበት ክፍል ውስጥ ነበር ትምህርታቸውን የሚከታተሉት።
የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ችግሩን ለአካባቢው ማኅበረሰብ ይፋ በማድረግ ማኅበረሰቡ ችግሩን ተመልክቶ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የአካባቢው ማኅበረሰብ ኮሚቴ በማቋቋም ድጋፍ ማስባሰብ ጀመረ።
አሠሪ ኮሚቴው ኅብረተሰቡን ከጎኑ በማድረግ፣ ምሁራንን በማማከር፣ የባለሀብቶችንም በር በማንኳኳት እና የሚገጥሙ ችግሮችን በመፍታት ወደ ሥራ በመግባት ትምህርት ቤቱ በአዲስ መልክ መሠራቱን ትምህርት ሚኒስተር አስታውቋል፡፡
በኅብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ አዲስ እና ለመማር ማስተማር ሚመጥኑ አምስት ሕንጻዎች ያሉት 25 የመማሪያ ክፍሎች መገንባት መቻሉም ታውቋል።