
ባሕር ዳር፡ መስከረም 22/2013ዓ.ም (አብመድ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህን ያሳወቁት እራሳቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማኅበራዊ ገጻቸው ነው።
“ዛሬ በኮሮናቫይረስ መያዛችን ተረጋግጧል፤ ለብቻችን ሆነን የምናገግም ይሆናል” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ሰው ሆፕ ሂክስ ቀደም ብሎ በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ትራምፕና ባለቤታቸው ራሳቸውን አግልለው ነበር ያለው ደግሞ ሲ ኤን ኤን ነው።
ትራምፕ የኮሮናቫይረስን ማጣጣላቸውና ተገቢውን ትኩረት አለመስጠታቸው ሲያስወቅሳቸው ነበር።