
የፌዴራል ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት አሻድሊ ሐሰን እና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች በተገኙበት ነው የኮማንድ ፖስቱ የሥራ ሪፖርት በግልገል በለስ ከተማ እየተገመገመ ያለው፡፡ በዚህም በቀጣናው እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ኮማንድ ፖስቱ እያከናወናቸው ያሉት ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ ለቀጣይ ተግባራትም አቅጣጫ ይቀመጥባቸዋል፡፡
በመተከል ዞን አምስት ወረዳዎች ማለትም ቡለን፣ ወምበራ፣ ድባጢ፣ ጉባ እና ዳንጉር ወረዳዎች የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በመከላከያ ሠራዊት የሚመራ ነው፡፡ ቀሪዎቹ ፓዌ፣ ማንዱራ እና የግልገል በለስ ከተማ አስተዳድር ደግሞ ኮማንድ ፖስቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በየወረዳዎች ዋና አስተዳዳሪዎች በበላይነት እንዲመሩት መወሰኑ ይታወሳል፡፡
መረጃው የመተከል ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ነው፡፡