
ባሕር ዳር፡ መስከረም 21/213ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ስፖርት ፌዴሬሽኖችና ኮሚቴዎች ጠቅላላ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
በጠቅላላ ጉባኤው ከሁሉም ዞኖች፣ ብሔረሰብ አስተዳደሮች የተውጣጡና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። የ2012 በጀት ዓመት የሥራ ክንውን ፣ የ2013 በጀት ዓመትና የቀጣይ 10 ዓመታት እቅድን በባሕር ዳር እየገመገሙ ናቸው።
በጠቅላላ ጉባኤው የሥራ ክንውንና እቅድ የሚገመገሙት ቮሊቦል፣ ባድሜንተን፣ ውሹ፣ ዳርት፣ ክብደት ማንሳት፣ ካራቴ፣ ጠረጲዛ ቴንስ፣ ጅምናስቲክ፣ ቼዝ፣ ወርልድ ቴኳንዶ፣ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ፣ መስማት የተሳናቸው፣ እጅ ኳስ፣ ቦክስ፣ ሜዳ ቴንስ እና ጤናና አካል ብቃት ፌዴሬሽኖች ናቸው።
ጉባኤው በቀጣይ አራት ዓመታት በ16 ፌዴሬሽኖች በአመራርነት የሚሠሩ እጩዎችን ይሰይማል ተብሎ ይጠበቃል።
በክልሉ በቀጣይ አስር ዓመታት የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ማስፋፋት፣ ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ መያዝ፣ የስፖርት ተሳትፎን ማሳደግ፣ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት፣ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ማስፋትና ስፖርታዊ ጨዋነትን ማጎልበት በሚሉ አበይት ተግባራት በትኩረት ለመሥራት ፌዴሬሽኖቹ እቅድ ይዘዋል።
ዘጋቢ፦ ግርማ ተጫነ