
ባሕር ዳር፡ መስከረም 21/213ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከሚታደምባቸው ዓመታዊ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የግሸን ደብረ ከርቤ የንግሥ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።
በዓሉ ለክልሉ የቱሪዝም ዕድገት የራሱ ጉልህ ድርሻ ያለው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ የሚታደምበት ነው።
ከመላው ኢትዮጵያ በርካታ ምዕመናን የሚታደሙበት የግሸን የንግሥ በዓል ከባለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ከኤርትራም በርካታ ምዕመናን መገኘት ጀምረዋል፤ ዘንድሮ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተሳታፊዎች ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም።