በሎንደን የሚኖሩ የወልድያና አካባቢዋ ነዋሪዎች ለኮሮናቫይረስ ሕክምና አገልግሎት የሚዉል ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

120

ባሕር ዳር፡ መስከረም 21/213ዓ.ም (አብመድ) በድጋፍ የተበረከቱት ቁሳቁስ ዋጋቸው 118 ሺህ ብር የሚሆኑ የሙቀት መለኪያ፣ የፊት መሸፈኛ ማስክ፣ የሕክምና ማስክ፣ የጤና ባለሙያዎች ሙሉ አካል የሚሸፍኑበት አልባሳት ናቸው፡፡

የተላከውን ዕርዳታ ያስረከቡት አቶ ወርቁ ተሾመ “ሁላችንም በመተባበርና ራሳችንን በመጠበቅ ለወገኖቻችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባል” ብለዋል፡፡

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ያካባቢው ተወላጆች ወረርሽኙ የሚሳድረውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እያደረጉት ላለው ጥረት ምሥጋና ያቀረቡት የወልድያ ከተማ ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን ኅብረተሰቡም ከወረርሹኙ ራሱን ለመከላከል ትኩረት እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ባለ ዓለምየ -ከወልድያ

Previous articleየኢትዮጵያ የማስታወቂያ ሥራ ማኅበር ተመሠረተ፡፡
Next articleበሀገሪቱ የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶችን በማስወገድ የህዝቡን የአንድነትና የአብሮነት እሴቶች ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ።