መንግሥት ከውጪ የሚያስመጣው ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ በከፊል ሊመረት ነው፡፡

419

መንግስት በዜጎች ላይ የኑሮ ውድነት እንዳይፈጠር በድጎማ ከውጪ ከሚያሥገባቸው መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን መካከል አንዱ ፓልም የምግብ ዘይት ነው።

ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ዘይቱን ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ ለማምረት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ አድማሱ ይፍሩ እንዳሉት ፌቬላ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ደብሊው ኤ የዘይት ማምረቻና ማከፋፈያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሸሙ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና አል ኢምፔክስ ዘይት ማምረቻ የተባሉት አራት ፋብሪካዎች ናቸው ዘይቱን ለማምረት ፍቃድ የተሰጣቸው፡፡

እነዚህ ኩባንያዎች የምርት ሂደታቸውን በቅርቡ እንደሚጀምሩ የገለጹት ዳይሬክተሩ ለግብዓትነት የሚጠቀሙበትን የዘይት ድፍድፍ ከውጪ ለማስገባትም ከብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ ማግኘታቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

Previous articleኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከወጪ ንግድ 400 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዷል።
Next articleበኦሮሚያና አፋር ክልሎች በአዋሽ ተፋሰስ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ አጋጠመ።