ሦስት ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ የታቀደበት ‘’ገበታ ለሃገር’’ ይፋ ተደረገ።

388

በሚገኘው ሃብት ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ በሚቀጥለው ዓመት ይለማሉ ተብሏል፡፡

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/ 2012 (አብመድ) የገበታ ለሃገር መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለኢትዮጵያ ብልጽግና አሻራቸውን የሚያኖሩበት ነው ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) “ገንዘብ፣ እውቀት እና ጉልበት በማሰባሰብ ተፈጥሮን ሳናውክ ለዜጎችም ለውጭ ቱሪስቶችም የምትመች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን” ብለዋል፡፡

በገበታ ለሃገር መርሃ ግብር በጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንታት የVVIP እና VIP የተከፈለበት የእራት ግብዣ ይኖራል፡፡

VVIP 10 ሚሊዮን ብር፣ VIP ደግሞ 5 ሚሊዮን ብር ይከፈልበታል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ብልጽግና ውስጥ ሁሉም ዜጋ አሻራውን እንዲያኖርም በኢትዮ-ቴሌኮም አማካኝነት የአጭር የጽሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ ይዘጋጃል፡፡

ዲያስፖራውም ድጋፍ እንዲያደርግ ገንዘብ የሚሰበሰብበት አካውንት ይከፈታል ተብሏል፡፡

በጥቅሉ ከገበታ ለሃገር ቢያንስ 3 ቢሊየን ብር ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚገኘው ሃብትም ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ በሚቀጥለው ዓመት ይለማሉ ተብሏል፡፡

ገበታ ለሃገር ገበታ ለሸገር ከአዲስ አበባ ተሻግሮ በመላው ኢትዮጵያ የሚሰፋበት ነው ሲል ፋብኮ ዘግቧል፡፡

Previous articleየኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከ 97 ሚሊዮን ብር በላይ ውዝፍ እዳ ለጎንደር ከተማ አስተዳደር እንዲከፍል የፍርድ ቤት ውሳኔ ተላለፈ።
Next articleዘላቂ ሠላም ለማስፈን በጥናት ላይ ተመሥርቶ እየሠራ መሆኑን የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ።