ድርጅቱ ለአውሮፕላን ማረፊያና ለቢሮ አገልግሎት ከ2002 ዓ·ም እስከ 2012 ዓ·ም ድረስ ሲጠቀምበት ለነበረው ቦታ 97 ሚሊዮን 584 ሺኅ 125 ብር እንዲከፍል በፍርድ ቤት ተወስኖበታል።
የኢትዮጵያ ኤርፓርቶች ድርጅት የጎንደር አፄ ቴዎድሮስ ኤርፖርት አስተዳደር ለ10 ዓመታት የተጠቀመበትን የቦታ ኪራይ ውዝፍ እዳ ነው እንዲከፍል የተወሰነበት።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድርጅቱ የቦታ ክራይ አለመክፈሉን በማረጋገጡ ለተጠቀመበት ቦታ በግብር ህጉ ስሌት መሠረት እንዲከፍል መወሰኑን ከከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።