በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ ሳምንት ብቻ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ መግዛታቸውን ኤምባሲው አስታወቀ።

158

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 8/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሕዳሴ ግድቡን የመጀመሪያ ውሃ ሙሊት ምክንያት በማድረግ በሳምንት ውስጥ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ መግዛታቸውን ኤምባሲው አስታውቋል።

የግድቡ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን በማስመልከት በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው የአንድ ሳምንት የቦንድ ሽያጭ መርሀ ግብር ነው ኢትዮጵያውያኑ 1 ሚሊዮን 15 ሺህ ብር የሚያወጣ ቦንድ የገዙት።

የቦንድ ሽያጩ “የታላቁ ሕዳሴ ግድባችን የውሃ ሙሌት መጀመር ታላቅ የምሥራች ነው፤ ለግድቡ መጠናቀቅ የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን” በሚል መሪ ሀሳብ ከነሐሴ 3 እስከ7 ቀን 2012 ዓ. ድረስ ነው የተካሄደው።

በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በ2012 በጀት ዓመት ብቻ 7 ሚሊዮን 395 ሺህ አምስት መቶ ብር የቦንድ ግዥ መፈጸማቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Previous articleሩሲያ ይፋ ያደረገችው ክትባት ውጤታማ ስለመሆኑ አለማረጋገጡን ዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
Next article“ከፊል ደስታ ከፊል ሐዘን ላይ ብንሆንም ደስታችን አመዝኗል።” የኢንጂነር ስመኘው ቤተሰቦች