መሪን በንቃት መምረጥ ሥልጡንነት ነው።

9

 

ወልድያ: ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ መርሳ ምርጫ ክልል የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

የመርጦ 01 ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት ገንዘብ ሲሳይ የምርጫ ካርድ ማውጣት እና በቀጣይ የሚወክለንን መምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታችን ነው ብለዋል።

ይህን መብታቸውን ለመጠቀምም የምርጫ ካርድ በወቅቱ በግንባር ቀደምነት እንዳወጡ ነው የተናገሩት። ቀኑ ሲደርስም በቀጣይ ይመራኛል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።

በምርጫ ጣቢያው ካርድ ሲያወጡ ያገኘናቸው ሌላኛው የቀበሌው ነዋሪ ፈንታው ይመር ሰው ተዘናግቶ እንዲሁ ከሚቆይ በወቅቱ ካርዱን መያዝ እንዳለበት መክረዋል።

ዛሬ ላይ ካርድ ይዞ መጠበቅ ተገቢ ነው ያሉት ፈንታው ይመር “በተመረጠ መንግሥት መመራት ሥልጡንነት ነው” ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ዛሬ ላይ ካርድን መያዝ ነገ መንግሥት ኾኖ ሀገር ሊመራ የሚገባን አካል ለመወሰን ቁልፍ ሂደት ነው ብለዋል።

ማንኛውም ዜጋ በወቅቱ ካርድ አውጥቶ የሚበጀውን መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል መብቱን ሊጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀረርን የምሥራቅ አፍሪካ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ያለመው የ”ዳር ሀረር” ፕሮጀክት።
Next article“በክርስቶስ ደም የተገዛውን የሰው ልጅ ክብር ማዋረድ አይገባም” ብጹዕ አቡነ አብርሐም