“ልሂድ በወልድያ በአዋጅ መንገሪያው ማክሰኞ ገበያ ሰው መገናኛው”

6
ወልድያ: መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዕለተ ማክሰኞ የሰሜን ወሎ ዞን እና የአጎራባች ክልል ነዋሪዎች ወልድያ ገበያ ላይ ሽያጭ እና ግዥ የሚያከናውኑበት ቀን ነው።
የወልድያ ማክሰኞ ገበያ ማኅበራዊ መስተጋብር የሚጠናከርበት፤ የተነፋፈቀ የሚገናኝበት ተናፋቂም ነው።
ይህ ገበያ:-
“ማክሰኞ ወልድያ ሰኞ ቆቦ ዋልኩኝ፤
የሸጋ ልጅ ጠረን እየተከተልኩኝ፤
ልሂድ በወልድያ በአዋጅ መንገሪያው
ማክሰኞ ገበያ ሰው መገናኛው” እየተባለ ተገጥሞለታል።
አሚኮ የትንሣኤ በዓል ግብይትን በሳምንታዊው ማክሰኞ ገበያ ተገኝቶ ቃኝቷል።
የእርድ እንስሳት በቂ አቅርቦት ቢኖርም ከልደት ገበያ ጋር ሲነጻጸር አንጻራዊ ጭማሪ ማሳየቱን ሸማቾች ነግረውናል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት መምሪያ ኀላፊ በላይ ገሰሰ የእርድ እንስሳት አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር መሠራቱን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article” ፖሊሶቻችን ሀገር እና ሕዝብ የሰጧቸውን አደራ መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ የሚጠብቁ መኾን ይገባቸዋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next article“በትንሣኤ በዓል የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር እየተሠራ ነው” ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ