
ደብረ ታቦር: መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ በወቅታዊ የልማት፣ የሰላም እና የጸጥታ ተግባራት ዙሪያ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የፋርጣ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ይርጋ ጌትነት በወረዳው ተፈጥሮ በነበርው የጸጥታ ችግር ቀሳዊ ውድመት መድረሱን አንሰተዋል።
ጠላት የግጭት ጊዜን በማራዘም የክልሉ ሕዝብ በሰላም እጦት እንዲተክዝ በማድረግ እና መሠረተ ልማቶችን በማውደም የጥላቻ ድርጊቱን መፈጸሙንም ተናግረዋል።
ከጦርነት ለመውጣት ኅብረተሰቡ የጠላትን ሴራ በጋራ መታገል እንደሚገባው ገልጸዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም በሃሳብ የበላይነት በማመን ከመገዳደል በመውጣት እና በመመካከር የእናቶችን ለቅሶ ማስቆም እንደሚገባ ተናግረዋል። ከትምህርት ገበታ ውጭ የኾኑ ልጆች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም በ አንስተዋል።
ጫካ የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ መቀበል እንዳለባቸውም ጠይቀዋል።
የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኅላፊ ሲሳይ ዳምጤ ክልሉ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከግጭት እንዳይወጣ ጠላት ሢሠራ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
መንግሥት ለሕዝቡ ዋስትና በመኾን የሕግ ማስከበር ሥራን ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
የጠላት ኃይሎችን እኩይ ተግባር በመቀልበስ የተረጋጋ ክልል እና ሀገርን ለመገንባት ኅብረተሰቡ እና የጸጥታ መዋቅሩ በቅንጅት እየሠሩ መኾናቸውንም አንስተዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫን በሰላም ለማስሄድ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ እንደኾነም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
