
አዲስ አበባ: መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የክልል መሪዎች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን አዳአ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ማሳን እየጎበኙ ነው።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ጌቱ ገመቹ መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት በክልሉ ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በክልሉ ባሌ እና ሌሎች አካባቢዎች ስንዴን በስፋት ማልማት መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ይህ ለውጥ በክልሉ የምግብ ዋስትና ችግር የነበረባቸው አርሶ አደሮች ፍጆታቸውን ከመቻል ባሻገር ወደ ትርፍ አምራችነት እንዲሸጋገሩ አድርጓል ነው ያሉት።
በ2011/12 የምርት ዘመን በ7 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ብቻ ተጀምሮ የነበረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን ላይ ወደ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ማደጉን ገልጸዋል፡፡
ከ150 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርትም ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት። በ2017/18 ዓ.ም የመኸር እርሻ ደግሞ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ማሳን በስንዴ በመሸፈን 109
ሚሊዮን ኩንታል ተገኝቷል ብለዋል።
ይህም በበጋ ስንዴ የተገኘው ስኬት ዘርፉን ከዝናብ ጥገኝነት ማላቀቅ እንደሚቻል ያመለክታል ነው ያሉት።
መሪዎቹ በክልሉ አዳአ ወረዳ የአፕል፣ የአቮካዶ እና የሙዝ ኩታገጠም፣ የክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ዝግጅትን እየጎበኙ የሚገኙት።
ዘጋቢ፦ ኢብራሂም መሃመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
