የአጣዬ ከተማ ወጣቶች የጸና አቋም ይዘው ለሰላም እየሠሩ ነው።

6

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች ከአጣዬ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) “የአጣዬ ከተማ ወጣቶች ለሰላም የጸና አቋም ያላቸው በመኾኑ ከአካባቢው የመንግሥት መዋቅር ጋር እየተባበሩ ሰላማቸውን ማጽናታቸውን አረጋግጠናል” ብለዋል።

በቀጣይ የከተማው ወጣቶች ሰላማቸውን በመጠበቅ በሚሠሩ የልማት ተግባራት ላይ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስረድተዋል።

በቀጣይ በከተማ አሥተዳደሩ ወጣቶችን ተሳታፊ ያደረጉ ሥራዎችን ለመተግበር እንደሚሠራም አብራርተዋል። ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር የተጀመረው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤሊያስ አበበ የአጣዬ ከተማ ወጣቶች በሰላም እና በአብሮነት የሚታወቁ ናቸው፤ አሁንም አንድነትን ጠብቀው ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሁለቱ የአጎራባች ዞኖች መሪዎች ተቀራርበው በመሥራታቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ቀጣናው የሰላም ቀጣና መኾኑንም ተናግረዋል።

የአጣዬ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች በበኩላቸው ለከተማቸው ሰላም የማይናወጥ አቋም እንዳላቸው ተናግረዋል። ከመንግሥት እና ከጸጥታ መዋቁሩ ጋር ተቀራርበው እየሠሩ መኾኑንም አረጋግጠዋል።

በከተማ አሥተዳደሩ እየተሠሩ ያሉ የልማት ተግባራት አበረታች መኾናቸውንም ነው የገለጹት። በሥራ ዕድል ዘርፍ ተጠቃሚ እየኾኑ መኾኑንም አንስተዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ይፋ ኾኑ።
Next article“ሀረር የሰላም ተምሳሌት ከተማ ናት ” ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ