
ባሕር ዳር: መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀስ የነበረው ፍቅሩ ሙሉዬ እና ጓደኞቹ የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
በአቀባበል መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ እዝ አዛዥ
ሜጀር ጀኔራል ተስፋየ አያሌው ፍቅሩ ሙሉዬ ቀደም ሲል በሀገር መከላከያ ውስጥ እንደነበር አስታውሰዋል። እርሱ እና ጓደኞቹ የሰላም አማራጭን ተቀብለው በመምጣታቸው እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
የአማራ ሕዝብ የጦርነት ቀጣና መኾን የለበትም ያሉት አዛዡ ሌሎችም የሰላም አማራጭን እንደሚቀበሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበለው ፍቅሩ ሙሉዬ ጦርነት ለማንም አይበጅም ብሏል። የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ሰላም መምጣታቸውንም ገልጿል።
ከላሊበላ ከተማ አሥተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በጫካ የሚገኙ ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
