የአማራ ክልል አድማ መከላከል ፖሊስ- የማይበገረው የሰላም እና የልማት ዘብ!

7
​ባሕር ዳር፡ መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጽናት የሚቆም ለሕዝብ ደህንነት የሚተጋ እና ለክልሉ ሰላም ዋስትና የኾነው የአማራ ክልል አድማ መከላከል ፖሊስ የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በንቃት፣ በቆራጥነት እና በታማኝነት እየሠራ ይገኛል።
​የክልሉን ሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ለመጠበቅ አድማ መከላከል ፖሊስ የዝናብና የፀሐይ መፈራረቅ ሳይበግረው ቀን ከሌሊት በንቃት ተሰማርቶ እየሠራ ነው።
አድማ መከላከል ከመከላከያ ሠራዊት እና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር ባለው ቅንጅት፣ በክልሉ በሁሉም አቅጣጫዎች አስተማማኝ ሰላም የማስፈን ሥራውን ያለመበገር አጠናክሮ ቀጥሏል።
​የሕዝብን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ በሚያደናቅፉ እና የክልሉን ሕልውና በሚፈታተኑ ሕገ ወጥ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል። የሕግ የማክከበር ሂደቱ በስኬት እየተከናወነ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የጥፋት ኃይሎች አቅም እየደከመና ሕዝቡ ወደ ቀድሞው መደበኛ ኑሮው እየተመለሰ ይገኛል።
​መጪው ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ ያለምንም ስጋት እንዲከናወን የጸጥታ ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ዝግጁነት ላይ ነው።
ሰላም የልማት መሠረት እንደመሆኑ፣ የዜጎችን ነፃነትና ደህንነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ዘመቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
​የክልሉ ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም እያሳዩት ያለው ድጋፍ ለተገኘው ውጤት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። ይህ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ለሰላም መጽናት እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ተላልፏል። መረጃው የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article
Next articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማካሄድ ጀመረ።