“የአባት ክትትልና የልጅ ጥረት ያፈራው ድንቅ ውጤት”

50

 

ደሴ: መጋቢት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዛሬ የተማሪዎች ምረቃ ዋንጫዎችን እና ሜዳሊያዎችን የግሏ ያደረገችው እየሩስ ብርሃኑ በብዙዎች ዘንድ አድናቆት እየተቸራት ይገኛል።

ተማሪ እየሩስ ብርሃኑ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የትምህርት ዘርፍ 3 ነጥብ 97 በማምጣት የሁለት ዋንጫ እና የወርቅ ተሸላሚ ኾናለች።

ከዚህ የበለጠ ጠንክራ ለተጨማሪ ትምህርት ጥረቷን እንደምትቀጥልም ከአሚኮ ጋር በነበራት ቆይታ ገልጻለች።

ለውጤቷ መሳካት የወላጆቿ በተለይ አባቷ ከፍተኛ ክትትል ያደርግላት እንደነበር እና በማጠናከርያ ትምህርት የበለጠ ውጤታማ እንደኾነች ገልጻለች።

ዘጋቢ፦ ሳሙኤል ኪሮስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleምርጫ፣ ሰላም እና ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው፡፡
Next articleበጎንደር ከተማ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ ነው።