
ደሴ: መጋቢት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በጊምባ እና በመካነሰላም ግቢ በስድስተኛው ዙር 698 ተማሪዎችን አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 241 ሴቶች ናቸው።
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ 51A+ እና ስድስት A በማምጣት አራት ነጥብ በማስመዝገብ ተማሪ ቃልኪዳን ታዘብ ከተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ክፍል የማዕረግ እንቁ ተሸላሚ ኾናለች።
“ተግቶ መሥራት የዛሬ ስኬቴ መሰረት ነው” ያለችው ተማሪ ቃልኪዳን በውጤቷ ደስተኛ መኾኗን ገልጻለች። በዩኒቨርሲቲው ቆይታዋ የመምህራን እና የወላጆቿ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው ጠቅሳለች። “በሙያዬ ሀገሬን እና ሕዝቤን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ” በማለትም ሀሳቧን አጋርታናለች።
ተማሪ ቃልኪዳን ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከሁለቱም ግቢ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ አጠቃላይ የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ ኾናለች።
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሴኔትም ለዚህ ስኬቷ ተማሪ ቃልኪዳን በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት እንድታገለግል እና የትምህርት እድል እንድታገኝ ወስኗል።
ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
