የተገኘውን ሰላም በማጠናከር እና የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ በዓሉን ማክበር ይገባል።

10
ከሚሴ፡ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በከሚሴ ከተማ ተከብሯል።
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ በመረዳዳት እና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ መኾን እንዳለበት አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የሃይማኖቱ ተከታዮች ገልጸዋል።
በተለይ የረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የዒድ ሶላት መስገጃ ቦታ ምላሽ በማግኘቱ መደሰታቸውንም አንስተዋል።
የከሚሴ ከተማ ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም በረመዳን ወር የታየውን መተሳሰብ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
የከሚሴ ከተማን የቆየ የአብሮነት እና የመከባበር እሴት ይበልጥ በሚያጠናክር መልኩ በመደጋገፍ፣ በመተጋገዝ፣ የታረዙትን በማብላት እና በማልበስ በዓሉን ማክበር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ ለረጅም ጊዜ ሲጠየቅ የነበረው የመስገጃ ቦታ ምላሽ መሰጠቱንም ተናግረዋል። ሌሎች ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚሠራም አንስተዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ የከተማዋን ሰላም እና ልማት ከመንግሥት ጎን ኾኖ ሊያስቀጥል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ በዓሉን ስናከብር የተገኘውን ሰላም በማጠናከር፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እና በመረዳዳት መኾን አለበት ነው ያሉት።
ሰላማችን እና አንድነታችንን አጠናክረን በማስቀጠላችን ከሚሴ ከተማ ምሳሌ እንድትኾን ማድረግ ችለናልም ብለዋል።
ዘጋቢ፦መስዑድ ጀማል
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለሀገር አንድነት በአብሮነት መሥራት ይገባል።
Next article“የሀገሪቱን 50 በመቶ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኘው ግብርናው ነው” የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን