ለጽንፈኛው ቡድን ሊደርስ የነበረን ነዳጅ እና የሞተር ዘይት መያዙን የምሥራቅ እዝ አስታወቀ።

69

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለጽንፈኛው ቡድን ሊደርስ የነበረን 136 ጀሪካን ነዳጅ እና የመኪና ሞተር ዘይት ሊያስተላልፉ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውን በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ እዝ አስታውቀዋል።

በደብረ ታቦር ከተማ ዙሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እና የሞተር ዘይት ለጽንፈኛው ቡድን ለማቀበል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ግለሰቦቹ 136 ጀሪካን ነዳጅ እና የሞተር ዘይት በአንድ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጭነው ከደብረ ታቦር ወደ ወረታ መንገድ ሲወጡ ስምሪት በተሰጣቸው የሠራዊት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው።

መንግሥት ወቅታዊ የነዳጅ ሥርጭትን ለመፍታት የተለያዩ መፍትሔዎችን በማስቀመጥ እየሠራ ባለበት ሰዓት ችግሩን ለማባባስ በሕገ ወጥ መንገድ ነዳጅን በጀሪካን በማድረግ ለመሠወር ጥረት ቢያደርጉም ሊያመልጡ ግን አልቻሉም ተብሏል።

ከምሥራቅ እዝ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው
ምሥራቅ እዝ በተሰጠው ሕግ የማስከበር የግዳጅ ቀጣና ከአካባቢው የጸጥታ ኃይል እና ከሕዝቡ ጋር በመጣመር ሕገ ወጥ ድርጊቶችን የመከላከል ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጭልጋ እና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደሰላም ተመለሱ።
Next articleየፖለቲካ ፓርቲዎች ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠሩ መኾኑን ገለጹ።