ሀገር በትብብር ትገነባለች።

7

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም(አሚኮ)የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት “ለሰላም ዘብ እንቆማለን የልማት አርበኛ እንኾናለን” በሚል መሪ መልዕክት ከፌዴራል ተቋማት እና የልማት ድርጅት ሠራተኞች ጋር እየተወያየ ነው።

በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ አሁን ያለውን ሰላም ለማጽናት ሁልጊዜ መወያዬት እና መነጋገር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ልማት እና ሰላም የማይነጣጠሉ በመኾናቸው የማኅበረሰብን የልማት ፍላጎት ለማርካት ተቋማት የበኩላቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ተቋማት ለሰላም ዘብ፣ ለልማት አጋር መኾን እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የሰላም እጦቱ ከቁሳዊ ጉዳት ባለፈ በሥነ ልቦናዊ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ስለዚህ ለችግሩ ሁላችንም ገፈት ቀማሾች በመኾናችን በአንድነት ውስጣዊ ሰላምን ማጽናት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ከገጠመን ፈተናዎች ተምረን ለመሻገር ለመፍትሔው ትኩረት በመስጠት ወደ ነበረው ክብራችን እና ሰላማችን መመለስ ይገባናል ብለዋል።

ሰላምን በማጽናት የታቀደውን ልማት ለማሳካት በመሥራት የተሻለች ሀገር ለነገው ትውልድ ማስረከብ የዜግነት ግዴታ መኾኑን ገልጸዋል።

ሀገር በትብብር ትገነባለች ያሉት አስተባባሪዋ ክፍተቶችን በጋራ ሞልቶ፣ ሰላምን አስከብሮ የተጀመሩ የልማት ኘሮጀክቶችን ለማሳካት የፌዴራል ተቋማት በሚሠሩበት ተቋም ከአገልግሎት አሰጣጥ ባለፈ የልማት አምባሳደር መኾን እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ቀጣይ በሚደረገው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዶ ጽኑ ሀገር ለመገንባት የድርሻችን መወጣት ይገባናል ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)ከሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያዩ።
Next articleኪነ ጥበብ ኢትዮጵያዊነትን ለማጽናት እና ለማነጽ ሚናው ከፍተኛ ነው።