ወጣቶች ለሀገር ሰላም የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል።

8
ባሕርዳር፡ የካቲት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር “ለሰላም ዘብ እንቆማለን፣ የልማት አርበኛ እንኾናለን” በሚል መሪ ሃሳብ ከልዩ ልዩ የአደረጃጀት መሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ሰብለ ዘውዱ ወጣቶች ለሰላም የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች በትኩረት ሊሠሩ ይገባል ነው ያሉት።
ወጣቶች አባቶቻቸው ያስረከቧቸውን ሀገር ሉዓላዊነቷን በመጠበቅ፣ ኢኮኖሚውን በማሳደግ፣ በልማት እና በሰላም እንቅስቃሴ ላይ ንቁ ተሳታፊ በመኾን ሀገርን ማሳደግ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶችም በተለይም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተሳታፊ መኾን፣ ግንዛቤን መፍጠር እና ለምርጫው ስኬታማነት የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።
የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚተጉ ያነሱት ወጣቶቹ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ እንደሚሠሩም አስረድተዋል።
የቀጣይ የሀገር ሉዓላዊነት በወጣቶች እጅ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ሰላማዊ ምርጫ እንዲከናወን እንተጋለን ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleትክክለኛው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን/አሚኮ/ የፌስቡክ ገጽ 1.8 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት እና በእንግሊዝኛ እና አማርኛ ስሙ የተጻፈበት ነው።👇
Next articleየምርምር ውጤት ከጽሑፍ ባሻገር ወደ እርሻ ማሳ መውረድ አለበት።