ዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ዋጋ መቀነሱን የቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

4
አዲስ አበባ: የካቲት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቡና እና ሻይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ዋጋ እና የቀጣይ ሥራዎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ላይ ያላትን የቡና ምርት ለማሳደግ ጥራት እና መጠንን ማሳደግ ላይ መሠረት አድርጋ ሥትሠራ መቆየቷን አንስተዋል።
ባለፈው የ2017 በጀት ዓመትም 470 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ መላኩን አንስተዋል። በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ 600 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነውም ብለዋል።
እንደ ሀገር የቡና ላኪዎችን ቁጥር ለመጨመር እየተሠራ መኾኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ 2 ሺህ ላኪዎች ፈቃድ ያገኙ ሲኾን ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 500 ላኪዎች በቀጥታ ምርቶቻቸውን ለዓለም ገበያ እያቀረቡ እንደኾነም ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ የዓለም የቡና ገበያ ከነበረው 4 ዶላር ወደ 2 ነጥብ 8 ዶላር መውረዱን ነው የተናገሩት። ይህ ደግሞ ቡና ይጨምራል ብለው ምርትን የከዘኑ ምርት አቀራቢዎች ላይ ኪሳራ ያስከትላል ብለዋል።
ቡና ተመርቶ በተገቢው ሰዓት ለገበያ መቅረብ አለበት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ምርትን ከዝነው ያስቀመጡ አቅራቢዎች ምርታቸውን አሁንም ወደ ገበያ ማቅረብ ይኖርባችዋል ሲሉ ገልጸዋል።
አለም አቀፍ የቡና ገበያ አሁን ካለበት ዋጋም ሊቀንስ እንደሚችል አስረድተዋል። የቡና ምርት ከዝነው የሚያስቀምጡ ላኪዎች የበለጠ ኪሳራ ሳይደርስባቸው ምርቱን ለገበያ እንዲያቀርቡም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ግዑሽ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የግማሽ ክፍለ ዘመን ጉዞ፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ድምፅ ለ50ኛ ጊዜ!”
Next articleየኩላሊት ጠጠር በሽታ ምልክት፣ ሕክምና እና መከላከያው