“ጥያቄያችን ለእውነትና ለፍትሕ ነው” የወልቃይት ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪዎች

12
ባሕር ዳር፡ የካቲት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “የመምረጥና የመመረጥ መብት ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው” በሚል መሪ መልእክት በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በቤት ሞሎ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የከተማው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት ለመንግሥት የሰላም ጥሪ ያላቸውን ጠንካራ ድጋፍ አሳይተዋል። የህወሃትን የዳግም የጦርነት ትንኮሳም አውግዘዋል። አካባቢያቸው የሰላም እና የልማት ማዕከል እንዲሆን ጠንክረው እንደሚሠሩ እና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ደጀንነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።
በሰልፉ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የከተማው ከንቲባ አለበል አንጋው እንደገለጹት ህወሃት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ በተለያዩ የአማራ አካባቢዎችን ዳግም ለመውረር እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። የሕዝቡን የመምረጥና የመመረጥ መብት ለማደናቀፍ እየሞከሩ ስለመኾኑም ገልጸዋል።
“ጥያቄያችን የእውነትና የፍትሕ ነው፤ ራስን የመሆንም ነው” ብለዋል።ሌሎችም የከተማ አሥተዳደሩ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ ተገኝተው የአንድነት፣ የሰላም እና የልማት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleምንጩ ያልታወቀ ሃብት ማለት ምን ማለት ነው ?
Next articleየማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲን የሚደግፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።