ከፍተኛ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ መሣሪያዎች በሆስፒታሎች ተደራሽ እየኾኑ ነው።

8

 

ባሕር ዳር: የካቲት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የኤም አይ አር ዘመናዊ ማሽን ለፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አድርጓል። በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) መንግሥት የጤና አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግ ጽዱ እና ምቹ የጤና ተቋም ከመገንባታ ባለፈ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንዲሠጥ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የኤም አር አይ ማሽኑ ውስብስብ የጤና ችግሮችን ለማከም የሚያግዝ የሕክምና መሳሪያ መኾኑንም አንስተዋል።

ማኅበረሰቡ በየአለበት የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጓል ነዉ ያሉት።

ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና መሳሪያዎች በሆስፒታሎች ተደራሽ ማድረግ ተችላል ብለዋል።

በቀጣይም በሁሉም ጤና ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ ይሠራል፤ በጤና ተቋማት አሠራሮችን በማዘመን ለማኅበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሠጡ መሥራት ይገባል ብለዋል።

ጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበወንጀል የተገኘ እና ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን የማስመለስ ሥራ በትኩረት እየተሠራ ነው።
Next articleበግጭት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚሠሩ ሥራዎች በትኩረት ሊከናወኑ እንደሚገባ ተገለጸ።