የዓድዋ ድል ሚስጢሩ የኢትዮጵያውያን የዓላማ ጽናት እና የሀገር ፍቅር ነው።

2
ባሕር ዳር፡ የካቲት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 130ኛው የዓድዋ በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉን በማስመልከት መልእክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞች ማኀበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን 130ኛው የዓድዋ በዓል የይቻላል እና የአሸናፊነት መንፈስ በማንገብ ማክበራችን ዳግም ኩራት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከዛሬ 130 ዓመታት በፊት የተፈጸመባትን ወረራ እና ግፍ በመራራ ተጋድሎ በማሸነፍ ነጻነቷን አጽንታ በአንድነት እንድትዘልቅ አድርጓታል ነው ያሉት።
የዛሬ 130 ዓመት የውጭ ወራሪ ኃይሎች በሕዝብ ላይ አስከፊ ጭፍጨፋ ቢፈጸሙም አልገዛም ባይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆ ብለው በመዝመት ወራሪውን በደም እና አጥንት መክተው መልሰዋል ብለዋል።
“ዓለምን ያስደመመው የዓድዋ ድል ሚስጥሩ ኢትዮጵያውያን የዓላማ ጽናት እና የሀገር ፍቅርን በመሰነቃቸው ነው” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። ድሉ ለዚህ ዘመን ተሻጋሪም ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለጠላቶች ሸብረክ የማትል የጀግኖች ምድር መኾኗን ሌሎችም ደግመው ደጋግመው ሊያስቡ እንደሚገባ ትምህርት የሰጠ ድል እንደኾነም ጠቁመዋል።
አሁንም ለጥፋት የሚታትሩ ኃይሎች ታሪካችንን ወደ ኋላ መለስ ብለው በመመርመር ራሳቸውን ከታሪካዊ ጥፋት እንዲያቅቡም ገንዝበዋል።
ኢትዮጵያን ወደሚመጥናት ከፍታ ለማሻገር ኀላፊነት አለብን ያሉት ፕሬዝደንቱ ትናንት ዓድዋ ላይ የተጎናጸፍነውን አስደናቂ ድል ዛሬም በሌሎች ተግባሮች አዲሱ ትውልድ ማስፋት እንደሚገባው መልእክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ እጣ ፋንታ በአዲሱ ትውልድ እጅ ነውም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleዓድዋ ዓለም የአሸናፊዎች መኾኗን አሳይቷል።
Next articleትውልዱ የዓድዋን ድል ለመድገም አንድነትን ማጠናከር አለበት።