“ዘመቻየ በጥቅምት ነው እና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ”

6
ባሕር ዳር: የካቲት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታሪካዊው የጦርነት የክተት አዋጅ መስከረም 07/1888 ዓ.ም ተለፈፈ፣ ነጋሪቱም ተጎሰመ።
ሕዝቡም ጨርቄን፣ ማቄን ሳይል በአራቱም ማዕዘን አቤት ንገሥ ኾይ ብሎ አውራው እንደ ተነካ ንብ የተመመበት፤ የጥቁሮችን የይቻላል መንፈስ በዓለም ያነገሠ አዋጅ ነው የዓድዋ የክተትጥሪ።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ ትምህርት ክፍል መምህሩ ተስፋው አበባው የአጼ ምኒልክ የክተት አዋጅን ሲገልጹ አዋጅ በዓለም ታሪክ በጣም አጭር እና ሀገርን አንድ ያደረገ በውስጡ ብዙ መልዕክት ያለው ነበር ብለዋል።
በሀገሪቱ በአራቱም ማዕዘን ሕዝቡን ለጋራ ዓላማ ያጸና እንዲኹም የያዘው ቁም ነገር ሠፊ ትርጉም ያለው ለሀገር መስዋዕትነት መክፈል እንዳለበት ያሳዩበት እንደነበር ገልጸዋል።
አዋጁ በውስጡ በያዛቸው ሀተታዎችም ድንቅ የመሪነት ጥበብን፣ ምጥን ያሉ የጋራ ጭብጥ ያላቸው እና ተስፋ ሰጭ መልዕክቶችን በግልጽ አስቀምጧል” ነው ያሉት።
“እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ ሀገር አስፍቶ አኖረኝ፤ እኔም እስካኹን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ ከእንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለእኔ ሞት አላዝንም…”።
በዚህ ሃሳብ በሃይማኖታቸው የማይደራደሩ እና በፈጣሪ ያላቸው ፍጹም ታማኝነት አሳይተዋል። ለሀገረ የሚከፈል መዋትነት ተገቢ ነዉ ብለዉ ያመኑበት፤ ለሀገር ፍቅር መስዋዕት እስከመኾንን ለሕዝቡ ያስተማሩበት እና የሳቸውን መንገድ እንዲከተል የቀሰቀሱበት ነውም ይላሉ መምህሩ።
“ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም” ይህ ንግገራቸው ደግሞ ለሀገራቸው አርቆ አሳቢ የኾኑት ንጉሥ በፈጣሪ ያላቸውን እምነት ወደ ፊትም እንደማያሳፍራቸው በአዋጁ ያስረዱበት እንደኾነም ገልጸዋል።
“ሀገር የሚያጠፋ፤ ፈጣሪ የሰጠንን ሀገር ባህር አልፎ ባሕልን፣ ሃይማኖት እና የሀገር ሉዓላዊነትን የሚያጠፋውን ጠላቱን እንዲፋለም ቁልጭ አድርገው ያስረዱበት ነው ብለዋል። በጋራ እንነሳ ያሉበት እንደኾነም ነግረውናል።
የሀገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም፤ አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም ሲሉ ጥበብ በተሞላበት፤ በአርቆ አሳቢነት የተናገሩት እና የሕዝቡን የሀገር ፍቅር የተረዱበት ንግግር ነው ብለውታል መምህሩ።
“ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ፤ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚስትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘንህ እርዳኝ” በማለትም ሁሉም ማኅበረሰብ በሚችለው አቅም በሚችለው ለሀገሩ አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት የተናገሩት ንግግር ነው ብለዋል።
ከጸሎት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል የሀገር ፍቅር ያነጹበት ነው ይላሉ ምህሩ። ተገቢነት፣ አካትችነት እና ወቅታዊነት ያለው መልዕክት ነው ብለዋል።
“ዘመቻየ በጥቅምት ነው እና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት ወሎ ወረኢሉ ላይ ከተህ ላግኝህ “ያሉት
የዘመቻውን ጊዜ መቼ እና የት፣ እንዴት እንደኾነም በግልጽ በምጥን አገላለጽ እና በቁጥብ ቃላት አስተላልፈዋል።
ዓደዋ የካቲት 1888ዓ.ም ታሪክ በአለም አደባባይ እንደ ንጉስ የወርቅ ካባ የለበሰበት፤ በጥቁር ሕዝቦች ምድር እንደሀውልት ተገንብቶ፤ በደማቸው ተጽፎ ሕያው እና ዘላለማዊ ቅርስ ታንጿል ብለዋል። ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች! በወቅቱ የክተት ጥሪ ሰምተው ዓይነ ስውራን ሳይቀር ሀገራችን የምናይበት ዓይን አለ ያሉበት እና የሀገር ፍቅራቸውን ገልጸዋል ብለዋል።
“ታሪክ ከማውራት ባለፈ ባለንበት ዘመን ለሀገራችን ምን ታሪክ ሠራን ማለት ይገባልም” ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት የታላቁ የዓድዋ ድል ቀጥተኛ ወራሽ ነው” ኢንጅነር አይሻ መሐመድ
Next articleኪነ ጥበብ ለዓድዋ