በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የደንበኞችን እርካታ 96 በመቶ ማድረስ ተችሏል።

1
ደብረ ብርሃን: የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ከተማ አሥተዳደሩ አስታውቋል።
የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ለአገልግሎት አሰጣጡ የሚያግዝ ሥልጠናን በደብረ ብርሃን ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ከተማዋ የመሶብ አንድ ማዕከሉን ለማስጀመር የሚያስችሉ አብዛኛውን ተግባራት መፈጸም ችላለች ብለዋል።
የተበታተነ አገልግሎት አሰጣጥን በቅንጅት ለመሥራት የሚያግዘው ይህ ማዕከል የከተማዋን ገጽታ የሚገነባ መኾኑን ገልጸዋል። የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ኅብረተሰቡን በታማኝነት ለማግኘት ማዕከሉ ቀዳሚ ተግባር ተደርጎ መሠራቱንም ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ እመቤት ምትኩ በክልሉ የመሶብ አንድ ማዕከል የደንበኞችን እርካታ 96 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅትም በሦስተኛ ዙር 25 የክልሉ ከተሞች ማዕከሉን እንዲያስጀምሩ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እየተደረገ መኾኑን አመልክተዋል።
ዘጋቢ፦ ብርቱካን ማሞ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ የተቋማትን አሠራር እያዘመነ ነው።
Next articleኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።