ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ በቁጭት መሥራት ያስፈልጋል።

3
ባሕር ዳር፡ የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና በቀጣይ የትምህርት ሥራዎች አቅጣጫ ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ በዘርፋ ፈተናዎች ቢኖሩም ባለፉት ስድስት ወራት ከትምህርት ማኅበረሰቡ እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መግባባት እና ተሳትፎ በማድረግ ለጥራት ተስፋ ሰጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በዚህም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከትምህርት ገበታ ውጭ የነበሩ ተማሪዎችን በመመለስ በትምህርት ገበታ የተገኙ ተማሪዎችን ቁጥር 60 በመቶ ማድረስ ተችሏል ነው ያሉት።
ባለፉት ስድስት ወራት በተሠራው ሥራ 7 ሺህ አዳዲስ የመማሪያ እና የአሥተዳደር ክፍሎች ያላቸው ከ218 በላይ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።
ዘግይተው ወደ ትምህርት ቤት የመጡ ተማሪዎችንም የማጠናከሪያ ትምህርት እና የአዳር ጥናት እንዲከወን በማድረግ ተወዳዳሪ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መኾኑን አንስተዋል። በቀጣይም ሁሉንም ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ እና ውጤታማ ለማድረግ በቁጭት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የዞን እና የወረዳ መሪዎች እንዲሁም ባለ ደርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleዜጎች የመምረጥ መብታቸውን በአግባቡ መጠቀም አለባቸው።