“ዓድዋ ለኢትዮጵያውያን የተሰጠ የነጻነት ስጦታ ነው” የጸጥታ አካላት

15
ባሕር ዳር: የካቲት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 130ኛው የአድዋ ድል በዓል ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ በሚል መሪ መልዕክት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከብሯል።
ዘንድሮ ለ130ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ከተለያዩ የጸጥታ መዋቅር መሪዎች እና አባላት እንዲኹም ከጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ጋር በመኾን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በዓሉን በፓናል ውይይት አክብሯል።
የከተማ አሥተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ሊዲያ ግርማ ዓድዋ ኢትዮጵያውያን ኢ-ፍትሐዊነትን በመታገል ለነጻነታቸው በአንድነት የታገሉበት መኾኑን ተናግረዋል። በዓሉን ስናከብር ለጸጥታ አካላት ክብር እና እውቅናን በመስጠት ሊኾን ይገባል ነው ያሉት።
የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል በልዩ ኹኔታ ውስጥ ኾኖ የሚከበር መኾኑንም ኀላፊዋ ገልጸዋል። በዓሉን በዓድዋ ድል መንፈስ እንደ ሀገር የሚካሄዱ ትላልቅ ኹነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቁ የጸጥታ አካላቱ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
“ዓድዋ ለኢትዮጵያውያን የተሰጠ የነጻነት ስጦታ ነው” ያሉት ደግሞ በዕለቱ የነበሩ የጸጥታ አካላት ናቸው። የሀገርን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሰላሟ እና ልማቷ የተረጋገጠች ሀገርን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ መኾናቸውንም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ቤተልሔም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየሰላም አማራጭን የተቀበሉ የቀድሞው የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ተወሰነ።
Next articleውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር ለብሔራዊ ጥቅም መከበር ወሳኝ ነው።