ተምሳሌታዊ ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ የቤት ሥራ ነው።

2
ደብረማርቆስ፡ የካቲት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ እንደ ሀገር የሚታዩ ድህነት፣ ኋላቀርነት፣ ግጭቶችን እና አለመግባባቶችን በማረቅ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታን ዕውን ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ ይገባል ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሰብዓዊ ልዕልናን፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ፣ ከተረጂነት እና ከግጭት አዙሪት በመውጣት ተምሳሌታዊ ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ የቤት ሥራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መኾናቸውን አስታውቀዋል።
የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ብልጽግና ፓርቲ እየተጋ ነው ብለዋል።
ኅብረተሰቡ በምርጫው ሂደትም በንቃት እንዲሳተፍ እና የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የክፍለ ከተማ መሪዎችም እንደ ሀገር ከተሳኩ ትልልቅ ፕሮጀክቶች በመማር የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዲጠናቀቁ በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሀሳብን በምርጫ ካርድ መግለጽ የዘመናዊ ሀገር እና ሕዝብ መገለጫ ነው።
Next articleምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን በትኩረት እየተሠራ ነው።