ሀሳብን በምርጫ ካርድ መግለጽ የዘመናዊ ሀገር እና ሕዝብ መገለጫ ነው።

2
ሁመራ፡ የካቲት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።
ለአንዲት ሀገር የተጠናከረ ሕዝብ እና የመንግሥት ግንባታ በሰላማዊ እና ሕጋዊ መንገድ ምርጫ ማድረግ እንደሚገባ በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ዮሀንስ አማረ ገልጸዋል።
ሀሳብን በምርጫ ካርድ መግለጽ የዘመናዊ ሀገር እና ሕዝብ መገለጫ መኾኑን ያነሱት አቶ ዮሀንስ በሰላማዊ መንገድ ምርጫውን ማካሄድ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የዞኑ ሕዝብ ከነጻነት እና ከለውጥ በኋላ በርካታ ጥቅሞቹ እየተከበሩለት መኾኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት የሕዝቡን ጥቅም እና መብት ለማረጋገጥ መሠራቱንም አንስተዋል።
የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የዞኑ ሕዝብ በምርጫው መሳተፉ ለበርካታ ዓመታት የነበረበትን የበጀት ችግር እንደሚቀርፍለት ተናግረዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዞኑ ሕዝብ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ያነሱት ኮሎኔል ደመቀ ለዞኑ ሕዝብ የወሰን እና ማንነት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አንስተዋል።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ገብረእግዚአብሔር ደሴ ምርጫ ለአንዲት ሀገር ወሳኝ ተግባር መኾኑን አንስተዋል።
ዘጋቢ፦ አምሳሉ አሞኘ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበአማራ ክልል በሦሥት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ30 ሺህ በላይ ተገልጋዮች ተስተናግደዋል።
Next articleተምሳሌታዊ ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ የቤት ሥራ ነው።