ምርጫው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በተግባር የሚረጋገጥበት እንዲኾን እየተሠራ ነው።

5
ደሴ፡ የካቲት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያዘጋጀውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ የማድረግ እና የማስተዋወቅ መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የሚመጥን ሀገር በቀል የፖለቲካ ፍልስፍና ይዞ እና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ትልም ነድፎ በመንቀሳቀስ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ የቻለ ፓርቲ መኾኑን አንስተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ዕውነተኛ ዴሞክራሲን ለማጽናት ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎችን በመከወን ተወዳዳሪነቱን በተግባር እያረጋገጠ ነው ብለዋል።
ምርጫው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በተግባር የሚረጋገጥበት እንዲኾን በልዩ ትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ እና ተአማኒ ኾኖ እንዲከናወን በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሸናፊ ዓለማየሁ ብልጽግና ፓርቲ በሀሳብ የላቀ ሀገራዊ ፓርቲ መኾኑን ጠቅሰዋል። በመደመር እሳቤ ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እያሻገረ ይገኛል ነው ያሉት።
ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ እና ተአማኒ ማድረግ ቀዳሚው ግብ መኾኑን ጠቁመዋል። ብልጽግና ፓርቲ ቀድሞ የነበሩትን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስብራቶች የጠገነ እንደኾነ ያብራሩት ኀላፊው ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ በአንድነት እና በጋራ ዕድገት ላይ የተመሠረተ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የሚያስችሉ ኹኔታዎችን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብ ድምጽ የሚከበርበት እና ፍትሐዊነት የሚነግሥበት እንዲኾን ሙሉ ዝግጅት መደረጉም በመድረኩ ተመላክቷል።
ዘጋቢ:- አበሻ አንለይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ወኪሎች እና ሞልትቡክ።
Next articleምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት የሚጣልበት ነው።