በሕገ ወጥ ድርጊታቸው በቀጠሉ ጽንፈኞች ላይ የሚደረገው ሕግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የምሥራቅ ዕዝ አስታወቀ።

13

 

ባሕር ዳር: የካቲት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ በተወሰደ እርምጃ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን መማረኩን የምሥራቅ ዕዝ አስታውቋል።

መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ባልተቀበሉ የጽንፈኛው ቡድን አባላት ላይ በሰሜን ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙርያ ከራከር በተባለው ቀበሌ ነው የተማረከው።

የምሥራቅ ዕዝ አንድ ሬጅመንት ባደረገው ስምሪት በጠላት ላይ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ መቻሉ ተገልጿል።

በዚሁ አካባቢ በተደረገው ፈጣን ኦፕሬሽን ሁለት መትረየስ ከነ ተተኳሹ፣ 6 የአር ፒጂ ላውንቸር ቅንቡላ ከ29 አቀጣጣይ ሸኝ ባሩድ ጋር፤ 6 ኤኬ ኤም ክላሽ እና 2 የቃታ መሣርያ ተማርኳል።

በተሰጠ ፈጣን የሥምሪት ዕቅድ መሠረት ወታደራዊ ሳይንስን እና ጥበብን በመጠቀም በጽንፈኛው ቡድን ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረስ ተችሏል ነው የተባለው።

ምሥራቅ ዕዝ ከክልሉ የጸጥታ ኃይል እና ከሕዝቡ ጋር በመጣመር በጥፋት ላይ በተሰማሩ ጽንፈኞች ላይ የሚያደርገውን ሕግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል። ዘገባው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተማሪዎችን ለሀገር እና ለክልል አቀፍ ፈተናዎች ብቁ ለማድረግ እየተሠራ ነው።
Next articleምርጫው ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል።