በጤና ሚኒስቴር በደቡብ ወሎ ዞን ሁለት ወረዳዎች መልሰው የተደራጁ የጤና ተቋማትን ርክክብ አካሄደ።

9

 

ደሴ፡ የካቲት 17/2018ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስቴር ከአውሮፓ ኅብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከዩኒሴፍ ጋር በአራት ዞኖች ለሚገኙ 35 የጤና ተቋማት የግንባታ ሥራ እና የሕክምና ቁሳቁስ እንዲሟላላቸው ተደርጓል።

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ሱሉላ ጤና ጣቢያ የግንባታ እና መልሶ የማደራጀቱ ሥራ ተጠናቅቆ ርክክብ ተደርጓል።

በተሁለደሬ ወረዳ በ46 ሚሊዮን ብር የተገነቡ እና ግብዓት የተሟላላቸው ሦሥት የጤና ተቋማት ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።

የጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ እንዲሁም የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የአውሮፓ ኅብረት ተወካዮች በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፦ሳሙኤል ኪሮስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአብሮነት በተደመረ እሳቤ ውስጥ ኾኖ ሀገር ለማቅናት ምርጫ ትልቅ መሳሪያ ነው።