
ደብረ ታቦር፡ የካቲት 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምርጫ የዴሞክራሲ አንዱ መገለጫ ነው። ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ ለማድረግ በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን የከተማዋ መሪዎች ተናግረዋል።
የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች በሰጡት መግለጫ ምርጫው በታቀደለት አግባብ እንዲከናወን ከኅብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መሥራት ወሳኝ መኾኑን ጠቁመዋል።
በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደበበ አክሎግ እንደገለጹት በከተማዋ የምርጫ ጣቢያዎችን ዝግጁ የማድረግ ሥራ እየተሠራ ነው።
ለመሪዎች እና ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎች መከናወናቸውን የገለጹት ኀላፊው ኅብረተሰቡ ለምርጫው እንዲዘጋጅ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ጠቁመዋል።
በደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኀላፊ እንዳልካቸው ዳምጠው ከቀደመው ምርጫ የተወሰዱ ልምዶችን በመጠቀም ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መኾኑን ተናግረዋል።
ምርጫው የዴሞክራሲ መገለጫ እና ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ የሚመለሱበት ሂደት በመኾኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ከማከናወን ጎን ለጎን የአካባቢውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ከደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ጋር በጋራ እየተሠራ መኾኑም ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
