
ደብረ ብርሃን: የካቲት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር “የወጣቶች መሪነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መልዕክት ውይይት ተካሄዷል።
በውይይቱ ላይ የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሰላም ተምሳሌት እንድትኾን የወጣቱ ሚና የጎላ ነው ብለዋል።
ሰላምን በመፍጠር፣ በማፅናት እና በሌሎች የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ላይ ለማተኮር የወጣቱ ሚና የላቀ መኾን እንደሚገባ ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል የሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ዘላለም አረጋ
የወጣቶች አንድነት እና ለለውጥ መሽቀዳደም በሁሉም ረገድ አበርክቶው የጎላ መኾኑን ተናግረዋል።
ነገሮችን በጥበብ መመርመር፣ በምክንያታዊነት እና በአስተውሎት የሚያምን ወጣት ሁሉን ይቀይራል ነው ያሉት።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ወጣቶችም ሰላም የሚጀምረው ከራስ በመኾኑ ሰላምን አፅንተው ለመቀጠል ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተቀራርቦ መነጋገር እና ውይይት ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መኾኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ዮናስ ታደሰ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
