
ባሕር ዳር: የካቲት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ “ከበሬ እርሻ በመላቀቅ ዘመናዊ የግብርና ሜካናይዜሽን አሠራርን በመከተል ምርትና ምርታማነትን እንጨምር” በሚል መልዕክት የትራክተር ሜካናይዜሽን ፌስቲቫል ተካሂዷል።
የቋራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አስማረ አንዳርጋቸዉ ፤ በቴክኖሎጅ የታገዘ የግብርና መካናይዜሽን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
በቀጣናዉ ካሉ የኢንቨስትመንት አካባቢዎች በተለየ በወረዳው ውስጥ ሰፊ ለም የሚታረስ መሬት እንዳለ ገልፀዋል።
ለባለሃብቶች ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አኳያ በቂ የመለዋወጫ አቅርቦት ችግርን በቅርበት እየተከታተልን፤ እየተወያየን መፍታት ይገባል የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
