
ደብረ ብርሃን: የካቲት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “በሴቶች ተሳትፎ የጸናች እና የበለጸገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት በደብረ ብርሃን ከተማ ከሴቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በሚኒስትር ማዕረግ የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ትርጉም እና የሕጎች ሕገ መንግሥታዊነት ክትትል ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ፍሬሕይወት ዱባለ እንዳሉት ብልጽግና ሴቶችን ከዳር ተመልካችነት ወደ ተሳታፊነት ያሳደገ የፓርቲ ሥርዓትን ለመፍጠር እየሠራ ነው።
ፖሊሲ ከመቅረጽ ጀምሮ አተገባበሩን በመቆጣጠር በሴቶች ተጠቃሚነት ላይ ውጤታማ ሥራ እያከናወነ መኾኑንም ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኢሌኒ ዓባይ ሴቶችን በተገቢው ማሳተፍ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ነው ብለዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ሴቶች ከመራጭነት ባለፈ በተመራጭነት እና በአሥተባባሪነት እንደሚሳተፉም አንስተዋል።
ምርጫውን ሙሉ ለማድረግ ሴቶችን ማብቃት፣ ማሳተፍ እና ወደ መሪነት ማምጣት ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
