
ገንዳ ውኃ: የካቲት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ከአካባቢው ከሰላም አስከባሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
ሰላምን ለማስከበር ከዚህ ቀደሙ በተሻለ መንገድ ለመሥራት ዝግጁ መኾናቸውን የውይይቱ ተሳታፊ ሰላም አስከባሪዎች ተናግረዋል።
የጸጥታ ኃይሉ ሰላምን ለማስፈን እና ለማረጋገጥ ከሌሎች የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞላ ገስጥ የጸጥታ መዋቅሩ የሕግ የበላይነትን ለማረጋጥ ከምንግዜውም በላይ መሥራት እንዳለበት ገልጸዋል።
በተለይ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን በመከላከል በኩል በርካታ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት። የጸጥታ ኃይሉ የተሰጠውን ኀላፊነት በታማኝነት እና በቅንት መወጣት አንዳለበትም ኀላፊው አስገንዝበዋል።
የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አብዱልከሪም ሙሐመድ “የጸጥታ መዋቅሩ በአቅምም ኾነ በሥነ ልቦና ከወዲሁ ዝግጁ መኾን እንዳለበት” ተናግረዋል።
ቀጣናውን ሰላም በማድረግ የውስጥ እና የውጭ ባንዳ ጠላትን ለመከላከል በተጠናከረ መልኩ ኃይሉ ግዳጁን መወጣት አለበት ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!ሀ
