
ደብረ ታቦር: የካቲት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር መሪዎች በወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኀላፊ እንዳልካቸው ዳምጠው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአካባቢው መውጣቱን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን አንስተዋል።
ከጥምር ጦሩ ጋር በመተባበር ግጭቱን ማክሸፍ መቻሉን አንስተው የፀጥታ ኃይሉን በአቅም ግንባታ እና በሥነ ልቦና የማጀገን ሥራ ከመሪዎች እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን ሰላምን በማስፈን ረገድ ባሉ ጥንካሬና ውስንነቶች ከሁሉም አመራሮች ጋር በመኾን መወያየታቸውን ተናግረዋል።
የከተማዋን ሰላም ለማስፈን አመራሩ በትጋት እንደሚሠራ ገልጸዋል።
ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመኾን የማጀገን፣ የማደራጀት እና የማገዝ ሥራ የአመራሩ ድርሻ መኾን አለበት ብለዋል።
በመንግሥት እና በግል የማኅበራዊ አገልግሎት ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት በአጭር ጊዜ ጠግኖ አገልግሎት ለማስጀመር እንደሚሠሩ አብራርተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
