የትምህርት ተደራሽነት ሽፋንን ከማሳደግ አኳያ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።

4

 

አዲስ አበባ፡ የካቲት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሰሜን ሸዋ እና የምሥራቅ ጎጃም የዞኖችን 2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የትምሕርት ሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ መኳንንት አደመ በበጀት ዓመቱ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የገጠሙ ፈተናዎችን ለማለፍ በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል ብለዋል።

ዋናው ተግዳሮት የኾነውን የትምህርት ተደራሽነት ሽፋን ከማሳደግ አኳያ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ከ11ሺህ በላይ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ከ88 በመቶ በላይ የሚኾኑትን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል ብለዋል።

የተመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ከማድረግ አኳያም 96 በመቶ አፈጻጸም መመዘገቡን ነው ምክትል ቢሮ ኀላፊው የገለጹት። ኀላፊው አክለውም በስድስት ወሩ የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል እና ለመምህራን የአቅም ማጎልበት ሥልጠና ከመስጠት አንጻር ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።

በተማሪዎች ምገባ፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ማስፍፍት እና የትምህርት ቤቶች ደረጃን ከማሻሻል አንጻርም ቢሮው የተሻለ ሥራ መሥራቱ ተገምግሟል።

የድጋፍ እና ክትትል ሥራው በጥብቅ ሥርዓት መመራቱን የገለጸው ቢሮው የዛሬው መድረክም በቀጣይ ያጋጠሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ ሴት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ለመመለስ እየተሠራ ነው።
Next articleበአማራ ክልል የጅፕሰም ምርት ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም ኾኗል።