
ሰቆጣ፡ የካቲት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምርጫ ዜጎች መሪዎቻቸውን ወይም ተወካዮቻቸውን በድምጽ የሚመርጡበት ሂደት ነው። ኢትዮጵያ በመጭው ግንቦት ወር 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ እና በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸው የዝቋላ፣ የድሃና እና የሰቆጣ ወረዳ መሪዎች ገልጸዋል።
መሪዎቹ ለዚህ የሚረዳ የቅድመ ዝግጅት ተግባር መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዋነኛ ማሳያ መኾኑን የገለጹት መሪዎቹ ወጣቶች ድምጻቸውን ከመስጠት ባለፈ የምርጫውን ሂደት ሰላማዊነት ነቅተው ሊጠብቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ እና ምክትል አሥተዳዳሪ ሹመት ጥላሁን ሕዝቡ በነፃነት መምረጥ እንዲችል አስተማማኝ ሰላም መኖር እንዳለበት ገልጸዋል።
ምርጫ ለምርጫ ቦርድ ብቻ የሚተው ሳይኾን ሁሉም ዜጋ በጋራ የሚሳተፍበት ብሔራዊ ተግባር መኾኑንም አውስተዋል።
ዘጋቢ ፦ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
