
ባሕር ዳር: የካቲት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአርጆ ድንጋይ መፍጫ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአርጆ ድንጋይ መፍጫ ፋብሪካ፤ ከውጭ ሲገባ የነበረውን የተፈጨ ድንጋይ ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላት በኢትዮጵያ የዘርፉ የኢንደስትሪ ልማት ዐቢይ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ፋብሪካው ለሲሚንቶ፣ ለብረት እና ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪዎች አስፈላጊ ጥሬ ግብዓቶችን ያቀርባል ነው ያሉት። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን በማረጋገጥ የኢንደስትሪ ልማትን እንደምታሳድግ ማሳያ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
