
ባሕር ዳር: የካቲት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ሃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነው ብለዋል።
በምዕራብ ወለጋ ገንጂ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና የግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ፕሮጀክቱ ለትምህርት፣ የመንገድ ልማት፣ የጤና ተቋማት እና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታን የማነቃቃት አቅም አለው ነው ያሉት።
በጉብኝታችን ወቅት እንደተመለከትኩት የፕሮጀክቱ ፋይዳ በአንድ የተወሰነ ብቻ ሳይኾን የአካባቢውን ማኅበረሰብ የበለጠ ለልማት በማነሳሳት ከፍ ያለ ሚናውን እንደሚያስቀጥል እምነቴ የፀና ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
