
ባሕር ዳር: የካቲት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰውን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር፤ ለግል ጥቅም በማሰብ ሰውን በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር እንዲገባ፤ ከሀገር እንዲወጣ፣ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ግዛት የማስተላለፍ ድርጊትን የሚያጠቃልል ዓለም አቀፋዊ ወንጀል ነው፡፡
ወንጀሉ በዛቻ፣ በኃይል፣ በማገት፣ በመጥለፍ፣ በማታለል ወይም ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም ሊፈጸም ይችላል። በዚህ ሂደት በርካታ ዜጎችን ለኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ የሚዳርግ፤ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ለሞት የሚዳርግ ጉዳይም ነው።
የዚህ ወንጀል ሰለባ የኾኑት ባለታሪካችን አቶ አዛናው አያናው በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በ2016 ዓ.ም ልጃቸው በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ታፍኖ እንደተወሰደባቸው ለአሚኮ ተናግረዋል።
ልጃቸውን አፍነው ከወሰዱት በኋላ አዘዋዋሪዎች “ወደ ሊቢያ ልናሻግረው ነው፤ ገንዘብ አስገባልን፤ የማታስገባ ከኾነ እንገለዋለን” በሚል ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንዳደረሱባቸው ይገልጻሉ።
አቶ አዛናው እንደሚናገሩት የልጃቸውን ሕይወት ለመታደግ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል። ለዚህም ያላቸውን ሀብት ንብረት ሽጠዋል። ከዘመድ እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ሳይቀር ለምነው የልጃቸውን ሕይወት ለመታደግ ጥረዋል። ብዙ መስዋዕትነትንም ከፍለዋል። በየዙሩ ለሚቀባበሉት ሕገ ወጥ ደላሎች ከ4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ መክፈላቸውን በቁጭት እና በሀዘን ስሜት ነግረውናል።
ልጃቸውን ከሞት ቢታደጉትም ለቤቱ ማብቃት ግን አልተቻለም። ልጃቸው በከፍተኛ እንግልት ከቤቱ ከወጣ ከ2 ወራት ስቃይ በኋላ ወደ ሊቢያ ልከውታል። የከፋ የሥነ ልቦና ጫናም እንደደረሰበት ነው የነገሩን።
አቶ አዛናው እንደገለጹት የወንድማቸው ልጅም በተመሳሳይ ሀገር ሰላም ብሎ ሥራውን ከሚሠራበት ቦታ ታፍኖ ከፍተኛ ገንዘብ ተጠይቆበት በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ወደ ሊቢያ ሄዶ ቀርቷል።
በኢትዮጵያ ወንጀሉን ለመከላከል እና ወንጀል ፈጻሚዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ አዋጅ ቁጥር 1178/12 ወጥቶ በሥራ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ አዋጅ እንደተደነገገው:-
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
