
ባሕር ዳር: የካቲት 7/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በኅብረቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ሌሎች እንግዶች የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና የታሪክ ስህተት መኾኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ።
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ጸሐፊው የአፍሪካ ጥንካሬ የሚመነጨው በራሱ በሚተማመን እና በተባበረ ሕብረት መሆኑን ተናግረዋል።
አሕጉሪቱ በዓለም አቀፍ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ የዓለም አቀፉን ተቋም ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል መኾኑን ጠቅሰው፤ ስለ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ውሳኔ በሚተላለፍበት ጠረጴዛ ዙሪያ አፍሪካ የግድ መገኘት እንዳለባት አጽንኦት ሰጥተዋል።
አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚገባትን ድምፅ እንድታገኝ የሚደረገውን ጥረት ድርጅታቸው እንደሚደግፍም አመልክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
