“ጣሊያን ከአፍሪካ ጋር መተባበር እንጅ መርዳት አትፈልግም” የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሚሎኒ

7

አዲስ አበባ፡ የካቲት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው የሚካሄደው ”ዘላቂ የውኃ አቅርቦት እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ መልዕክት ነው።

የጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሚሎኒ በኅብረቱ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ትብብር በተመሳሳይ ኃይሎች መካከል የሚደረግ ሁነት ነው ብለዋል።

እኛ አፍሪካን የምናያት በዚህ ልክ በመኾኑ መርዳት ሳይኾን የምንፈልገው መተባበር ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

በዚህ መንፈስ በጤና እና በግብርና ጉዳዮች ተካሂዶ ውጤታማ የነበረው የጣሊያን አፍሪካ ጉባኤ እንዲሳካ ትብብር ያደረጉትን ጓደየኛ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)ን አመሰግናለሁ ነው ያሉት።

ጣሊያን አፍሪካ ያለመችውን ግብ እንድታሳካ ታግዛለች ብለዋል። በተለይ በመሠረተ ልማት ወደኃላ የቀሩ አካባቢዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እና የሰላም ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ታግዛለች ብለዋል።

አንደ አውሮፓ ኅብረትም ኾነ አንደጣሊያን ስደት መብት ቢኾንም አፍሪካውያን ባሉበት ማገዝ እንጂ በሜዲትራኒያን ባሕር ሕይወታቸውን እንዲያጡ አንፈልግም ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ ኢብራሂም ሙሐመድ

አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ የቀጣናዊ ትስስር ጉዞዋን እያፋጠነች ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ግብር የዜጎች አርበኝነት የሚገለጽበት ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)