
አዲስ አበባ፡ የካቲት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እነተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ሌሎች እንግዶች የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ጉባኤው የሚካሄደው ”ዘላቂ የውኃ አቅርቦት እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ መልዕክት ነው።
መሪዎቹ የሚመክሩት 48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አሥፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ሥብሠባ ላይ ውይይት በተደረገባቸው አጀንዳዎች ላይ መኾኑ ተገልጿል።
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ እስከ የካቲት 8/2018 ዓ.ም ይቆያል።
ዘጋቢ፦ ኢብራሂም ሙሐመድ
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
